AMHARA TRANSITIONAL COUNCIL (ATC)
  • Home
  • About ATC
  • ዋና ዋና የዐማራ ስብስቦች
  • ሳምንታዊ የATC ርዕሰ አንቀጽ
  • የዕለቱ ዋና የሶሻል ሜድያ ትኩረት
  • የATC ምክር ቤት ውሳኔዎች
  • በዐማራ ፋኖ ሳምንታዊ ዉሎዎች
  • የበይነመረብ ትግል አስተባባሪ
  • Diplomacy
  • Political coordination
  • Finance & Logistic
  • Research & Development
  • Transitional Justice
  • Coalitions Building
  • Fano coordination
  • ATC Central Committee
  • Public Relation
  • Socio Economic Crisis
  • ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
  • ATC Organogram
  • DEIT (IT & Engineering)
  • More
    • Home
    • About ATC
    • ዋና ዋና የዐማራ ስብስቦች
    • ሳምንታዊ የATC ርዕሰ አንቀጽ
    • የዕለቱ ዋና የሶሻል ሜድያ ትኩረት
    • የATC ምክር ቤት ውሳኔዎች
    • በዐማራ ፋኖ ሳምንታዊ ዉሎዎች
    • የበይነመረብ ትግል አስተባባሪ
    • Diplomacy
    • Political coordination
    • Finance & Logistic
    • Research & Development
    • Transitional Justice
    • Coalitions Building
    • Fano coordination
    • ATC Central Committee
    • Public Relation
    • Socio Economic Crisis
    • ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
    • ATC Organogram
    • DEIT (IT & Engineering)
AMHARA TRANSITIONAL COUNCIL (ATC)
  • Home
  • About ATC
  • ዋና ዋና የዐማራ ስብስቦች
  • ሳምንታዊ የATC ርዕሰ አንቀጽ
  • የዕለቱ ዋና የሶሻል ሜድያ ትኩረት
  • የATC ምክር ቤት ውሳኔዎች
  • በዐማራ ፋኖ ሳምንታዊ ዉሎዎች
  • የበይነመረብ ትግል አስተባባሪ
  • Diplomacy
  • Political coordination
  • Finance & Logistic
  • Research & Development
  • Transitional Justice
  • Coalitions Building
  • Fano coordination
  • ATC Central Committee
  • Public Relation
  • Socio Economic Crisis
  • ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
  • ATC Organogram
  • DEIT (IT & Engineering)

DIPLOMACY - የዓለም አቀፍ ግንኙነት አስተባባሪ

አግባብ ያለው ኮሚቴ የስራ መመሪያን በማዘጋጀት የቡድን መሪዎችን በመሰየምና አስፈላጊ ቅድመ

ዝግጅት በማጠናቀቅ የዐማራውን ፍላጎት በሚመለክት በአለም ዓቀፍ ደረጃ መካሄድ ያለባቸውን

የግንኙነት ስራዎች ከፍተኛ ግፊት በሚያሳድር ስልት ዘርዝሮ መውጣትና ወደ መርሃግብር ለመቀየር

በዚህ ዘርፍ ጠንካራ ልምድ ያላቸውን በሚያሳትፍ ደረጃ ህዝባዊ ድፕሎማሲን ያከናውናል። 

በሳምንቱ ከዲፕሎማሲ ኮሚቴ ውይንም ከሌላ ተቋም የወጡ ዐማራ ተኮር መግለጫዎችና ምልከታዎች

የዐማራ አለም ዓቀፍ አላያንስ ካውንስል ዲፕሎማሲ


የአማራ ህዝብ ትግል መንግስታዊ ስልጣን ከተቆጣጠሩ በከፍተኛ ደረጃ ሃብት፣ የጦር መሳሪያ እና የውጭ መንግስታት ድጋፍ ካላቸው ሃይሎች ጋር የሚደረግ መራራ ትግል ነው። ትግሉ የተሳካ እንዲሆን፣ በሁሉም መስክ በሚገባ የታሰበበት፣ የተደራጀ፣ የታቀደ፣ መሆን ይኖርበታል። ስለዚህም አማራን ለማጥፋት እኩይ አላማ ይዘው ለተነሱ አካላት ምላሽ በሚገባ በታሰበባቸው እስታራቴጂዎችና እውቀትን፣ ጥበብን እና አቅምን አሰናስኖ መፈጸም ያስፈልገዋል። ማንኛውንም የአማራ ህዝብ እና የትግሉ አጋሮች እና ደጋፊዎች የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም የሚችል ቀልጣፋና ቁርጠኛ የትግል አቅጣጫዎች መካከል የዲፕሎማሲ ዘርፍ አንዱ ነው።


ባሁኑ ወቅት የአብይ አህመድ አገዛዝ እና ወያኔ በማካሄድ ላይ ያሉትን ተጨባጭ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻዎች ምላሽ የሚገባ የአማራ የህልውና ማስከበሪያ ዲፕሎማሲ እስትራቴጂ መዘርጋትና በዕለታዊ መርሃ ግብር መፈጸም ወሳኝ ግዳጅ መሆኑ መረዳት አያስቸግርም። በህልውና አደጋው አሳሳቢ ተፈጥሮና የትግሉን የተለያዩ ባህሪዎች የተነሳ በውጭ ሃገራት የሚገኙ የአማራ ህዝብ ህልውና አሳስቧቸው በግልና በቡድን ጥረት የሚያደርጉ አካላት በፍጥነት ውይይት ማድረግ፣ ወቅቱን የሚመጥን የጋራ ግንዛቤ ላይ በመድረስ፤ በፍጥነት ማከናወን ያለባቸውን የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ማስቀመጥ ተገቢ ነው። በአማራ ህልውና ላይ ያንዥበበውን አደጋ በዋነኛነት ማስቆም ብሎም ከምንጩ ማድረቅ። የራሱ የአማራ ህዝብ ሃላፊነት መሆኑን በመረዳት፣ የውጭ ሃይሎች የማይገባ ተጽእኖ ላይ ግልጽ አቋም መውሰድ አስፈላጊ መሆኑንም ከዚሁ ጋር መገንዘብ ያስፈልጋል። 


ከዚያም በመቀጠል በዚህ ፈታኝ ወቅት እንደ ሃገር የቅርብ ጊዜ የዲፕሎማሲ ውድቀቶችን ለመጠቆም ያህል፥ 


  • ሃገሪቱ የምእራባውያን በተለይ የአሜሪካ መንግስትና የአውሮፓ መጫወቻና መቀለጃ በመሆኗ  ከጎረቤት ሃገራት ጋር በቋሚ የጋራ ጥቅምና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት መፍጠርና ማስቀጠል አለመቻል፣
  • እየተቀየረ ያለውን የጂኦ ፖለቲካ እውነታ ግምት ውስጥ ማስገባትና አለማችን ከአንድ የበላይ ልዕለ ሃያል መንግስት ተጽዕኖ ወደ የብዝሃን ሃያላት ማእከል ጎራ መከፋፈሉ ያመጣውን የሚዛን ለውጥ አለመረዳት፣
  • ቋሚነት የሌለው የሚዋዥቅ ማንንም አጋር ማድረግ የማይችል፣ በችግር ወቅት በወዳጅነት የቆሙትን እና ሲቆሙ የኖሩትን የቅርብና የሩቅ አጋር ሃገራትን መክዳት፣
  • በመጨረሻም ወደኋላ የማንመለስበትን ታሪክ መልሶ መላልሶ ለፖለቲካ ፍጆታ ከመጠቀም ይልቅ ላንዴና ለመጨረሻ  ክፍለ አህጉራዊ ህዝብን ማዕከል ያደረገ intra-regional social society  በመመስረት የጎረቤት ሃገራት ይበልጥ እንዲያቀራርቡና የጋራ ሃብታቸውን በጋራ እንዲያበለጽጉ የሚያደርግ ፖሊስን ቀርጾ በጽናት መስራት ያለመቻል ናቸው። 

ከላይ የተጠቀሱትን የሃገሪቱን ዲፕሎማሲያዊ መሰረታዊ ችግሮች በመገንዘብ የአማራ ህልውና ትግል ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ረቀቅ ሃሳብን በማዳበር በተገቢው መጠን ለህዝባዊ ውይይት ማቅረብና በጠንካራ የዲፕሎማሲያዊ ግብረሃይል መመራት ይኖርበታል።

የዐማራ ምክር ቤት የዲፕሎማሲ ንኡስ ኮሚቴ ዓምድ

AMHARA TRANSITION COUNCLE (ATC)

Copyright © 2024 Amhara (AIA)  - All Rights Reserved.

Powered by GoDaddy

Announcement

Welcome! Check out my new announcement.

Learn more

This website uses cookies.

We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.

Accept