የአማራ ህልውና ምርምርና ስርጸት የስራ ዘርፍ መግቢያ
በርካታ የዐማራ ምሁራንና ልሂቃን ከዚህ ቀደም የዐማራን ማህበረሰብ ጥቃትን አተኩሮ ለመመልከትና በወሳኝ የህልውና መድረኮች ላይ እንኳን በጠንካራ አቋም ለራሳቸው ንኡስ ማህበረሰብ ቆሞ ለመሞገት አለመቻላቸው ወድኋላ የስከፈለውን ዋጋ ዘግይተውም ቢሆን ተረድተዋል።
የአማራ ካውንስል ትምህርትና ጥናት የስራ ዘርፍ የአማራን እሴቶች ባህላዊና ማህበረሰባዊ አንትሮፖሎጂ ቅርጽና ይዘት ያገናዘበ የውስጥና የውጭ የፖለቲካ አካሄዶችን እግር በግር በመከታተል በዓይነ ቁራኛ የሚጠብቅና እየመጡ ያሉ ችግሮችን ወዲያውኑ ምላሽ የሚሰጥ ንቁ ትውልድ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ ፕሮግራም ለመዘርጋት ጥረት ማድረግ ይጠበቅባታል። የዛሬው ትውልድ የአማራ ህልውናን መጠበቂያ የፖሊሲ አቅጣጫ በመቅረጽ ከህጻናት እስከ አዛውንት ለተካታታይ ትውልድ ተገቢ የሆነ የንቃተ ህሊና ግንዛቤ ማዳበሪያና ትምህርትና ጥናት ዝግጅትን በታሪክና በስነማህበረሰብ ባለሙያዎች የሚመራ ተቋም መመስረት ያስፈልገዋል ።
ስለሆነም ለዘመናት የዐማራውን በማህበረሰብ የላግባብ ተጠቂ እንዲሆን የደረጉ ትርክቶች ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የሃገር ውስጥና አለም አቀፋዊ ታሪካዊ ዳራዎችን በዝርዝር መዳሰስና በጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ የተመሰረተ ጥቆማ ለማድረግ ያስችለዋል። ካውንስሉ በቀጣይ በሚያደርገው የማስተባበር ተግባር የህትመትና የግንዛቤ ማዳበሪያ የትምህርትና የምርምር ስርጸት ስራዎችን ተቋማዊ በሆነ መንገድ በመምራት የዐማራ ምሁራንና ልሂቃን የተቆርቋሪነት ማማ ለይ እንዲወጡ ይጋብዛል። የካውንስሉ ምርምርና ጥናት ተቋም ይዘትና ዓላማ በሚከተሉት ዝርዝር አቅጣጫዎች መመልከት ይቻላል።
፩፡ በሃገር ውስጥ በአማራ ህልውና ላይ ስጋት ውስጥ የሚፈጥሩ ቡድኖችንና ተቋሞች መዘርዘርና ማስቀመጥ።
፪፡ በዐማራው ህልውና ላይ ስጋትና ጥቃትን የሚጋብዙና ያሚያቀነባብሩ ከኢትYኦጵያ ውጭ ያሉ ቡድኖችና ተቋሞችን ዘርርዝሮ በመተንተን ለዲፕሎማሲ ስራዎች አመቺ ሁኔታዎችን ማመቻቸት።
፫፡ ሃያላንና ተጽዕኖ ፈጣሪ ተቋሞችን በአማራ ማህበራዊ ፖለቲካና ሃገረ መንግስት ነባር ሚና ዙርያ ያላቸውን አሉታዊ ፖሊሲዎች ማሻሻያ እንዲያደርጉ የሚያበረታታ የፖሊሲ ጥናት ዝግጅት
፬፡ በዓላም አቀፍ ተቋማት ውስጥና በዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ውስጥ ወይንም ቅርበት ባላቸው ትውልደ አማራዎችን ማስተባበርና የሃገር አቀፍ ሽግግር ፍትህ አንዲሁም የሃገሪቱን ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ ከዓማራው ህልውናና ጥቅም አንጻር መርምሮ የፖሊሲ አቅጣጫ ግፊትን ለማሳደር የሚያስችል የጥናትና ምርምር ሰነድ ማዘጋጀት።