በእስካሁኑ የፋኖ ጥንታዊና ባህላዊ ጠንካራ አሰራር መሰረት የውስጥ አገዛዞች ወይንም የውጭ ወራሪዎች በበርካታው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ ሲያራምዱ ወይንም መሰረታዊ ነጻነትና ሉዓላዊነትን ሲዳፈሩ ከየቤቱ በጎበዝ አለቃ ተጠራርቶና ተደራጅቶ የሚመክት ጥንታዊ የህልውና ሰራዊት ነው። ከምተ ዓመታት በላይ በሚሻገረው የፋኖ ዝክረ ታሪክ በሰላም ጊዜ አራሽ ቀዳሽና አነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማራ መደበኛ የከተማና የገጠር የተሰማራ ነዋሪ ሲሆን የህልውና ወይንም የሉዐላዊነት ክተት ጥሪን ተከትሎ በአጭር ታጥቆና ቤተሰቡንና ጎረቤቱን ተሰናብቶ የሚተም ህዝባዊ የክብር ሰራዊት ነው።
በአሁኑ ሰዓት የአማራ ከተከታታይ ጥቃትና ህልውናውን የማፍረስ ሴራ የመታደግ አለምአቀፍ ድጋፍ የማስተባበር ተግባር በብቃትና በስኬት ለመወጣት የሚያስችል የተግባር እንቅስቃሴን በአውራጃ ደረጃ ከሚያያይዝ ማህበረሰባዊ መዋቅራዊ ስራ ጋር ተቀናጅቶ መሄድ ይኖርበታል። ይህን በሚገባ ለማከናወን በውጭና በሃገር ውስጥ ያሉ ካውንስሉ ታማኝ አባላትና ደጋፊዎችን በማካተት የአውራጃ አስተባባሪ ግብረሃይል ማዋቀር እንደሚያስፈልግ ይታያል።
1-የህዝብ አስተዳደርና ጸጥታ ጥበቃ
የመከላከያና በብርጌድ እዝ አመራሮች የፖሊስ አባላት እንዲሁም የደህንነት ሰራተኞች ግንዛቤን ለማሳደግ አፈና፣ እንግልት፣ መሰወርና፣ ግድያ ላይ እንዳይሳተፉ ማድረግ። በንጹሃን ግለሰቦች፣ አማኞችና ካህናትን ማሸማቀቅ፣ ያካል ጉዳትን የሚያደርሱ የወረዳና ክፍለ ከተማ የጸጥታ ጽህፈት ቤት ሰራተኞችን የሚከታተልና የፍርድ ቤት ክስ የሚያስተባብር ህዝባዊ ቡድን በወረዳ ደረጃ እንዲቋቋም ማበረታታት።
ይህንን ለማድረግ ተባባሪ የመከላከያና የፖሊስና የአስተዳደር ጽህፈት ቤት አባላት እንዲሁም ጠቃሚ ከሆኑ ህዝባዊ ድርጅቶች አባላትን በአካባቢ ደረጃ መለየትና ሚስጥራዊ ትብብር መፍጠር ናቸው።
2-የአማራ ፋኖ ዘርፍ
በአውራጃ ደረጃ የተመደቡ የፋኖ ተጠሪዎች የሚመለከታቸውን የፋኖ ቡድኖች አመራሮችን በመገናኘትና በመከታተል በሳምንት ሁለት ቀን ለካውንስሉ ዓለም አቀፍ የስራ ዘርፍ ክፍል ወቅታዊ ሁኔታዎችን በኢሜል ያቀርባሉ።
የአማራ ህልውና አስከባሪ ዓላማ መሳካት ጠንካራ ድጋፍ የሚሰጡ ግለሰቦችን እንዲሁም በስጋትነት የሚታዩ ሁኔታዎችን በልዩ የመገናኛ ዘዴ ለተጠሪ አካል በየእለቱ ያሳውቃሉ። በአውራጃ ደረጃ የሚሰሩ የፋኖ ተጠሪዎች ሳምንታዊ የዳሰሳ ስብሰባ ካውንስሉ ተዛማጅ የስራ አስፈጻሚዎች ስብስብ ጋር በቅንጂት ያካሂዳሉ ።