The Amhara International Alliance (AIA) will build international support for an Amhara Fano-centered sociopolitical transition in Ethiopia by offering advocacy and technical coordination across various areas, including public diplomacy, peace and stability, transitional justice, socioeconomic crisis management, publicity, and necessary logistics.
ከዐማራ አለም ዓቀፍ አላያንስ ማደራጃ ግብረ ሃይል በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ትውልደ ዐማራ ማህበረሰቦች የቀረበ የመጀመሪያዎቹን የዐማራ መማክርት ጉባኤ አለም ዓቀፍ አባላት ምርጫ ላይ ትውልደ ዐማራ ሁሉ እንዲሳተፍ የመጋበዝና የጥቆማ መርሃግብር ተደርጎአል፦
እራስዎን በዕጩነት መጠቆምም ሆነ ምረጡኝ የሚል ቅስቀሳ ይበልጥ ተቀባይነት ያለው አካሄድ ነው። ሆኖም ግን እባከወትን ከታች የተጠቀሱትን 3 መሥፈርቶች ያሞአላል / ታሞላለች የምትሉትን ዐማራ የሆነ / የሆነች እንዲጠቁሙን በጥሞና እንጠይቃለን።
፩) በዐማራ የህልውና ትግል ገንቢ ተሳትፎ እንደነበረውና የማያጠራጥር አቋም ያለው
፪) በቡድን ስራ የሚያምን / የምታምን ይህንን የሚያሳይ የከዚህ ቀደም አስተዋፅኦ የነበረው / የነበራት
፫) በAIA- ዌብ ሳይት https://amaracouncil.net ላይ የተቀመጠውን ዓላማ የሚደግፍና በሚኖርበት አካባቢ ያሉ አማራዎችን
ማስተባበር የሚችል በዕጩነት ሰው ለመጠቆም::
ከላይ የተጠቀሱትን የሃገሪቱን ዲፕሎማሲያዊ መሰረታዊ ችግሮች በመገንዘብ የአማራ ህልውና ትግል ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ እረቂቅ ሃሳብን በማዳበር በተገቢው መጠን ለህዝባዊ ውይይት ማቅረብና በጠንካራ የዲፕሎማሲያዊ ግብረሃይል መመራት ይኖርበታል።
አያሌ መስዋዕትነትን ከሚያስከፍል ድል ማግስት ብዙ የተለያዩ አላማና ዕርዮተ ዓለም ያላቸው ቡድኖች እና አደረጃጀቶች ለስልጣን ወደ ፊት ይመጣሉ። ነገር ግን ከፓለቲካ ቅድመ ዝግጅት ዕጦት የተነሳ በተጋድሎ የተገኘን ድል ተመልሶ እንዳይቀለበስ ቀደም ብለን በብልሃትና በሩቅ አስተዋይነት ላይ የተመሰረተ ርዕዮተ ዓለም መቅረፅ ይኖርብናል።
ከመቶ ዓመታት በላይ በሚሻገረው የፋኖ ዝክረ ታሪክ በሰላም ጊዜ አራሽ አነስተኛ ንግድ ላይ መደበኛ የከተማና የገጠር የተሰማራ ነዋሪ ሲሆን የህልውና ወይንም የሉአላዊነት ክተት ጥሪን ተከትሎ በአጭር ታጥቆና ቤተሰቡንና ጎረቤቱን ተሰናብቶ የሚተም ህዝባዊ የክብር ሰራዊት ነው።
ከላይ የተቀመጠው ትንታኔ አጥብቆ የሚያስገነዝበን የአማራና የሌሎች ን ኡስ ማህበረብ የኢትዮጵያ ዜጎች እየመጣባቸው ያለውን የህልውና ችግር በጊዜ በመረዳት የጋራ ውስጣዊ ጥንካሬን የሚፈጥር የህዝብ ግንኙነት ፕሮግራም ስራዎችን በተጠናና በተቀነባበረ ስልት ማካሄድ ይኖርባቸዋል።
የአማራ ካውንስል ትምህርትና ጥናት የስራ ዘርፍ የአማራን እሴቶች ባህላዊና ማህበረሰባዊ አንትሮፖሎጂ ቅርጽና ይዘት ያገናዘበ የውስጥና የውጭ የፖለቲካ አካሄዶችን እግር በግር በመከታተል በዓይነ ቁራኛ የሚጠብቅና እየመጡ ያሉ ችግሮችን ወዲያውኑ ምላሽ የሚሰጥ ንቁ ትውልድ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ ፕሮግራም ለመዘርጋት ጥረት ማድረግ ይጠበቅባታል።
ከዚህ ቀደም በበርካታ የአፍሪካ፣ የአውሮፓና የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ተፋላሚዎች ሃገራዊ ችግሮች ተጨባጭ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ የሽግግር ፍትህ ሂደትን ማድረጋቸው ይታወሳል። በተለይ በደቡብ አፍሪካ፣ በሩዋንዳ፣ በላይቤሪያ፣ ሴራሊዮንና፣ በኬንያ የነበረውን ባህርያት ትምህርታዊነትና አርአያነትን መመርመር ይቻላል።
የአማራ ህልውና በይነመርብ ቴክኒዮሎጂ የስራ ክፍል መግቢያ
ለበርካታ ዓመታት መቆየት የተስፋ ማጣት አኗኗር ሁኔታን ለመቀነስና በዚህ ቀውስ ውስጥ የሚያድጉ ህጻናት አካላዊና አእምሮአዊ ዕድገት፣ የስነልቦና ተጠቂነትን ለመቀነስ ከአስር ዓምት ያላነሰ የማህበራዊ ኢኮኖሚ ማስተር ፕላን ፕሮግራም ዝግጅት በውጭ ሃገር ያሉ የአማራ ተቆርቋሪዎች በስፋት ለማሰማራት ተገቢና ወቅታዊ የወገን ጥሪን ማስተጋባት ይኖርብናል።
በውጭ ሃገራት የሚንቀሳቀሱ የዐማራ ህልውና ትግል ድጋፍ ሰጪዎች ስብስቦች መካከል የሚኖር ጣምራ አሰራር ፍላጎት በተለይ በዚህ የፋኖ ተጋድሎ ወቅት እጅግ አስፈላጊነት በብዙዎች በኩል ጥያቄ አይኖረውም። ሆኖም የጣምራ አደረጃጀት ሂደትን፣ የአካባቢያዊ ቅርበት ስበትና በአሰራር ስለት ዙርያ በሰፊ ውይይት የዳበረ የጣምራ ድጋፍ ሰጪነት ፕሮግራም መዘጋጀት ይኖርበታል።
በአሁኑ ሰዓት የአማራ ከተከታታይ ጥቃትና ህልውናውን ማፍረስ ሴራ የመታደግ አለምአቀፍ ድጋፍ የማስተባበር በብቃትና በስኬት ለመወጣት የሚያስችል የተግባር እንቅስቃሴን በአውራጃ ደረጃ ከሚያያይዝ ማህበረሰባዊ መዋቅር ስራ ጋር ተቀናጅቶ መሄድ ይኖርበታል።
የየዐማራ ሽግ ግር ምክር ቤት ከጠቅላላ የዓላምችን ክፍሎች የተውጣጣ አንድ መቶ የሚደርሱ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ሲኖሩት ከፋኖ ድጋፍ ሰጪዎች በስተቀር እያንዳንዳቸው ቢያንስ አምስት ስማቸው በይፋ በተዘረዘረ የዐማራ ማህበረሰብ አንቂዎችና ኤሊቶች አዎንታዊ ድጋፍ ያገኙ መሆን ይኖርባቸዋል።
Send us a message or ask us a question using this form. we will do our best to get back to you soon!
AMHARA TRANSITION COUNCLE (ATC)
Copyright © 2024 Amhara (AIA) - All Rights Reserved.
Powered by GoDaddy
We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.